ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለስላም
አቶ ያሲን መሃመድ
የኮልፌ ቀራንዮ ከ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት
ኃላፊ
ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የበርካታ ዓለም ዓቀፍ ዲፕሎማቶች መቀመጫ፤ የሀገራችን ርዕሰ ከተማ እና 3ኛዋ የዲፕሎማቲክ ከተማ እንደ መሆኗ መጠን ደረጃዋን የሚመጥን ሰላም ፀጥታና የህግ የበላይነት ሊያስከብሩና ሊያረጋግጡ የሚችሉ ዘመናዊ የፀጥታና ህግ አስከባሪ ተቋማት ሊኖራት ይገባል፡፡
ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የክፍለ ከተማውንና የከተማውን የሰላምና የጸጥታ አስተዳደር ጉዳዮች የማስተዳደር እና ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ሃላፊነቶች ተቀብሎ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀ እንዲሁም ምልዓተ ህዝቡን በማሳተፍ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ቢሮው በአዋጅ የተሰጡትን ኃላፊነቶች ከሌሎች ህግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በከተማችን አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያትና አጋጣሚዎችን በመጠቀም ለመፈጸም ታቅደው የነበሩ የስርዓት አልበኝነት፤ የወንጀል፤ የሁከትና ብጥብጥ እና የሽብር ተግባራት እንዳይሳኩ ከማድረግ በተጨማሪ የሚከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ክብረ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ በማድረግ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡የክፍለ ከተማውንና የከተማችን የሰላም የጸጥታና የህግ ማስከበር ስራዎች በተቋም አቅም መፈጸም የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር እየተደረጉ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ ሆነው የከተማችን ሰላምና ጸጥታ ለማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጣቸው በየደረጃው የሚገኙ የቢሮው መዋቅር በሰው ሃይል ፤በግብዓት፤ በአሰራር እና በአደረጃጀት በማጠናከር ተልዕኮውን በተገቢው የሚፈጽም የህግ አስከባሪ ተቋም እንዲሆኑ ማድረግ ጊዜው የሚጠይቀው ሃላፊነት እንደ መሆኑ መጠን የክፍለ ከተማውንና የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ መላው የከተማችን ህዝብ እና ተቋማት በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማሳተፍ ከሚቻልባቸው ዘዴዎች መካከል ድህረ-ገጽ አንዱ እንደ መሆን መጠን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ድህረ-ገጽ በመጠቀም ሰላም፤ ጸጥታ እና ህግ ማስከበርን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በመሆን የዜግነት ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ::
አመሰግናለሁ !!
በክፍለ ከተማው ከ1ሺ በላይ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማው ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት አዲስ ለተመለመሉ እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብ እና የመስክ ስልጠና በዛሬው እለት የማስጀመሪያ መድረክ አካሂዷል፡፡
የክፍለ ከተማው ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ያሲን መሀመድ በዚህ ዙር በክፍለ ከተማው ከ1ሺ በላይ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የመስክ እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎችን በመውሰድ ስምሪት እንደሚያደርጉ ተናግረው ሰልጣኞች ከስልጠና በኋላ የአካባቢያቸውን ሰላም ከማጠበቅ፣ህገ ወጥነትን ከመከላከል አንፃር ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
በክፍለ ከተማው የዛሬ ሰልጣኞችን ጨምሮ ከ14ሺ በላይ ሰላም ሰራዊት አባላት የአካባቢቸውን ሰላም እያስጠበቁ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው በቀጣይ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን የተጣለበቸውን ኃላፊነት በትጋት እንዲቀጡ ጥሪ አቅርበዋል። see more
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት በ2016 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት የእውቅና መርሀ ግብር አካሄደ።
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት በ2017 በጀት አመት በ1ኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከክፍለ ከተማና ከ11ዱ ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ የፀጥታ አካላት፣የሀይማኖት አባቶች፣የሰላም ሰራዊት እንዲሁም የአጎራባች ክፍለ ከተሞችና አስተዳደሮች በተገኙበት የ2016 በጀት አመት አፈፃፀም እውቅና ሰጥቷል ። see more
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት በ2016 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት የእውቅና መርሀ ግብር አካሄደ።
በክፍለ ከተማው አስተዳደር ከ11ዱም ወረዳ የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት "ሀገር ወዳድነትና የሀገረ መንግስት ግንባታ " በሚል መሪ ቃል የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡
በኮንፍረንሱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ማንነት ፣የሀገራዊ ማንነት ግንባታ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ዙሪያ የመወያያ ሰነዶች ቀርቦ ውይይት ተካሔዶበታል። see more
ያለምንም የፀጥታ ችግር የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ የክፍለ ከተማው ሰላም ሰራዊት አባላት አስታወቁ።
የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት አከባበር ላይ የክፍለ ከተማው ሰላም ሰራዊት አባላት ውይይት አድርገዋል። በዓላቱ ትውፊታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባ አቶ አደም መሀመድ የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ምክትል የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል።see more
ተልዕኮ
የተቀናጀ የጸጥታ ጉዳዮች አስተዳደር እና የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ወንጀልን በመከላከል፤ የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ በሃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል መከባበርና መቻቻል እንዲሰፍን በማድረግ፤ የክትትል፤ ቁጥጥር እና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት፣ ነዋሪውንና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ባለቤትነት በማረጋገጥ ሰላም፣ ጸጥታና ደህንነቷ የተጠበቀ እና ህግና ስርዓት የተከበረባት ከተማ ማድረግ ነው፡
በ 2022 አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ ለኑሮ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና ማየት
የህግ የበላይነትን ማክበርና ማስከበር
ለላቀ ሰላምና ጸጥታ መትጋት
ታማኝነትና ተጠያቂነት
ተቋማዊ አጋርነት
ፍትሐዊነትና ሰብዓዊነት
ሚስጥር ጠባቂነት