ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለስላም
በክፍለ ከተማው ከ1ሺ በላይ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማው ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት አዲስ ለተመለመሉ እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብ እና የመስክ ስልጠና በዛሬው እለት የማስጀመሪያ መድረክ አካሂዷል፡፡
የክፍለ ከተማው ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ያሲን መሀመድ በዚህ ዙር በክፍለ ከተማው ከ1ሺ በላይ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የመስክ እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎችን በመውሰድ ስምሪት እንደሚያደርጉ ተናግረው ሰልጣኞች ከስልጠና በኋላ የአካባቢያቸውን ሰላም ከማጠበቅ፣ህገ ወጥነትን ከመከላከል አንፃር ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
በክፍለ ከተማው የዛሬ ሰልጣኞችን ጨምሮ ከ14ሺ በላይ ሰላም ሰራዊት አባላት የአካባቢቸውን ሰላም እያስጠበቁ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው በቀጣይ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን የተጣለበቸውን ኃላፊነት በትጋት እንዲቀጡ ጥሪ አቅርበዋል።
"ሀገር ወዳድነትና የሀገረ መንግስት ግንባታ " በሚል መሪ ቃል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሔደ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 03 /2017 ዓ.ም
በክፍለ ከተማው አስተዳደር ከ11ዱም ወረዳ የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት "ሀገር ወዳድነትና የሀገረ መንግስት ግንባታ " በሚል መሪ ቃል የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡
በኮንፍረንሱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ማንነት ፣የሀገራዊ ማንነት ግንባታ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ዙሪያ የመወያያ ሰነዶች ቀርቦ ውይይት ተካሔዶበታል።
ኮንፈረንሱን የመሩት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ ሰላም ሁላችንም እጅ ያለ በመሆኑ የሀገራችንን ሰላም መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አክለውም በከተማችን በርካታ ትላልቅ የልማት ስራዎች በመስራት ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ ያለ ሲሆን ልማቶች እንዳይደናቀፉ ሁሉም ለሰላም ዘብ ሆኖ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሁሉም ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም ተናግረዋል።
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በዜጎች ዘንድ የሚነሱ ጉዳዮችን በጋራ ውይይት ለመፍታትም መጠነ ሰፊ ስራ በመሰራትም ላይ እንደሚገኝም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለው ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ያሲን መሀመድ የተረጋጋችና ሰላም የሰፈነባት ሀገር ለመፍጠር እያንዳንዱ ዜጋ የጎላ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባውና ሀገር ወዳድ ትውልድ በመፍጠር ለሀገረ መንግስት ግንባታ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው ህብረብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት ፣አንድነታችንና አብሮነትን በማጠናከር ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሚናቸውን እንደሚወጡ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ ወጣቶች ፣ሴቶች ፣የኃይማኖት አባቶች ፣አባገዳዎች ፣የሰላም ሰራዊትና የእድር ምክር ቤት አባላት ፣ከነጋዴው ማህበረሰብ፣ እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት በ2016 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት የእውቅና መርሀ ግብር አካሄደ።
ጥቅምት 05/2017 ዓ.ም ኮልፌ ኮሙኒኬሽን
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት በ2017 በጀት አመት በ1ኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከክፍለ ከተማና ከ11ዱ ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ የፀጥታ አካላት፣የሀይማኖት አባቶች፣የሰላም ሰራዊት እንዲሁም የአጎራባች ክፍለ ከተሞችና አስተዳደሮች በተገኙበት የ2016 በጀት አመት አፈፃፀም እውቅና ሰጥቷል ።
በእውቅና መርሀ ግብሩ ተገኝተው የማጠቃለያ ሀሳብና የስራ መመሪያ የሰጡት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በክፍለ ከተማው አስተዳደር ከፀጥታ አካላት፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከሰላም ሰራዊትና ከመላው የህብረተሰብ ክፍሎች ተቀናጅቶ በጋራ በመሰራቱ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ተችለዋል ያሉ ሲሆን ሁሉም አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ ተናግረዋል ።
አቶ ንጋቱ በንግግራቸው እንደከዚህ ቀደሙ ግንኙነታችን አጠናክረን እጅ ለእጅ በመያያዝ በክፍለ ከተማው የሚስተዋሉ ህገ ወጥ ተግባራት በመከላከል ከስጋት የፀዳችና ሰላም የተረጋገጠባት ክፍለ ከተማ እንፈጥራለን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፏል ።
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ያሲን መሀመድ በበኩላቸው ባለፈው በጀት አመትም ሆነ በአንደኛ ሩብ አመት የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም የተሻለ አፈፃፀም ማምጣት ይገባናል ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ የ2017 በጀት አመት አንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም በአቶ ታፈሰ አዱኛ የሰላምና ፀጥታ መረጃ ስራ ሂደት አስተባባሪ አመካኝነት ቀርቦ ውይይት ተካሄደቦታል።
በመጨረሻም በ2016 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ባለ ድርሻ አካላት የፌደራልና የአዲስ አበባ የፀጥታ አካላት፣ሴክተር መስሪያቤቶች ፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ የሰላም ሰራዊት ተወካዮች እና ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን ወረዳ 04፣ 05 እና 01 ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆናል።
ያለምንም የፀጥታ ችግር የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ የክፍለ ከተማው ሰላም ሰራዊት አባላት አስታወቁ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን መስከረም 08/2017 ዓ.ም
የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት አከባበር ላይ የክፍለ ከተማው ሰላም ሰራዊት አባላት ውይይት አድርገዋል።
በዓላቱ ትውፊታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባ አቶ አደም መሀመድ የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ምክትል የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ምክትል ስራአስፈፃሚ አቶ ባዩ ሽጉጤ እንደገለፁት የሰላም ሰራዊት አባላት እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ የነበራቸውን አስተዋፅኦ በእነዚህ በዓላትም በመድገም በዓሉ በአብሮነትና በአንድነት እንዲከበር የአካባቢያችሁን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነታችሁን መወጣት ይገባችኋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የክፍለ ከተማው የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰኢድ መሀመድ ሁለቱም በዓላት ከእኛ አልፈው የአለም ቅርስ በመሆናቸው ኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነታችንን በማጠንከር በሰላምና በአብሮ ነት በጋራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ /ቤት ሀላፊ አቶ ያሲን መሀመድ እነዚህ የአደባባይ በዓላት እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ሰላምን በማስጠበቅ የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አለብን ያሉ ሲሆን እኛ ኢትዮጵያዊ የተሳሰርንና የተጋመድን መሆናችንን ለአለም ማሳየት አለብን ሲሉ ገልፀዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዓላቱ ከዚህ ቀደም እንደተከበሩ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
መጪው የመስቀልና የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከአጎራባች ሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን መስከረም 13/2017ዓ.ም
በዛሬው እለት መጪው የመስቀልና ኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ ፉሪ፤ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ተወካዮችና የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማው አስተዳደር አመራሮች፣የፌድራል ፖሊስ ፣የሁለቱ ክፍለ ከተሞች ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡
የመስቀልና የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የጋራ እቅድና አደረጃጀት በመፍጠር በዓሉ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር እንዲሁም የክፍለ ከተሞችን ግንኙነት ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑነ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማወያየት በበዓላቱ ወንድማመችነትና እህትማማችነትን በማጎልበት ህብረ ብሔራዊ እንድነትን በማጠናከር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
ከሁለቱ ክፍለ ከተሞች የተወከሉ አካላት እንደተናገሩት የመስቀልና ኢሬቻ ባዕላት በደማቅ ዝግጅቶች እንዲከበሩ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም የክፍለ ከተሞቹ የጋራ ግንኙነት በማጠናከር ህብረተሰቡም የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን አብሮ መስራት አስፈልጊ መሆኑን በውይይቱ ተገልጿል፡፡