ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለስላም
የቢሮው ስልጣንና ተግባር
የደንብ ማስከበር ባለሥልጣንን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
የብሔራዊ የፀጥታና የሰላም ፖሊሲን መሠረት በማድረግ የከተማውን የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳይ ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ከተማ አቀፍ ፖሊሲ ይቀርፃል፤ ስትራቴጂ ይነድፋል፤ ህግ ያመነጫል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
በፀጥታ ጉዳዮች የከተማው አስተዳደር ዋና የፀጥታ አማካሪ ሆኖ ይሰራል፤ ለፀጥታና ሰላም አስጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ተገቢ የሆነ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም እንደ አግባብነቱ ራሱ ወይም ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት የእርምት እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
የግጭት መንስዔዎችን በጥናት ይለያል፣ ግጭት እንዳይከሰት ይከላከላል፤ ሲከሰትም ባህላዊና ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ይፈታል፤
በከተማው ልዩ ልዩ ሀይማኖትና ቤተ-እምነት ተከታዮች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብነት ካላቸዉ የፌደራልም ሆነ የከተማው አስተዳደር አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤
በግጭት መከላከል፣ አያያዝም ሆነ አፈታት፣ በነዋሪው ደህንነት፣ ሰላም እና ፀጥታ አጠባበቅ ጉዳዮች ዙሪያ አግባብነት ካላቸው የፌደራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር እና ሌሎች አካላት ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ያደርጋል፤ እንደአግባብነቱ ችግሮችን በተናጠል ወይም በጋራ ይፈታል፤
ህግና ስርዓት መከበሩንና የህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት መጠበቁን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና በስውር የነዋሪውንና የመንግስትን ጥቅም ጉዳት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና ድርጅቶችን በመከታተል ነዋሪውንና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል
የተቀናጀ የጸጥታ ጉዳዮች አስተዳደር እና የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ወንጀልን በመከላከል፤ የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ በሃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል መከባበርና መቻቻል እንዲሰፍን በማድረግ፤ የክትትል፤ ቁጥጥር እና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት፣ ነዋሪውንና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ባለቤትነት በማረጋገጥ ሰላም፣ ጸጥታና ደህንነቷ የተጠበቀ እና ህግና ስርዓት የተከበረባት ከተማ ማድረግ ነው፡
በ 2022 አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ ለኑሮ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና ማየት
የህግ የበላይነትን ማክበርና ማስከበር
ለላቀ ሰላምና ጸጥታ መትጋት
ታማኝነትና ተጠያቂነት
ተቋማዊ አጋርነት
ፍትሐዊነትና ሰብዓዊነት
ሚስጥር ጠባቂነት