ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለስላም
አቶ ሙልጌታ ጎንፋ
የፅ/ቤት ሃላፊ መልክዕት
የክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በአዋጅ የተሠጠውን ተግባርና ሃላፊነት በመወጣት የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ እና ቅድመ-መከላከልን መሠረት ያደረገ ያሰራር ስርዓትን የማሳደርበ እና ይህን አልፈው የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የእርምት እርምጃዎች የመውሰድ ቅንጂታዊ ስራዎችን ማጠናከር፣አሰራሮችን በማዘመን ክፍለ ከተማችንን ከደንብ ጥሰት የፀዳች እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ማድረግ ነው፡፡
የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፤
1 በስሩ የሚገኙ የስራ አስተባባሪዎችን፣ ቡድኖች እና ባለሙያዎችን ያስተባብራል፣ ይመራል፤
2 በህግ የተሰጡትን የደንብ መተላለፎች የመከላከል፣ የመቆጣጠርና እርምጃ የመውሰድ ስራዎችን ይደግፋል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ ሲሆን የኦፕሬሽን ስራዎችን በጋራ ይሰራል፤
3 ከደንብ ማስከበር ጋር በተያያዘ የወጡና የሚወጡ አዋጅ፤ ደንብ፤ አፈጻጸም መመሪያዎች ስራ ላይ መዋላቸውን እና በተለያዩ ዘዴዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መሰጠቱን ይከታተላል ይቆጣጠራል፤
4 የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤትን ይደግፋል፣ ይከታተላል፣ አመራር ይሰጣል፤
5 የደንብ መተላለፍን በተቀናጀ መልኩ መከላከልና መቆጣጠር ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላትን እና ህብረተሰቡን የማሳተፍና የማደራጀት ስራን ያስተባብራል፣
6 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በስሩ ያሉትን ፓራሚሊተሪ ሰራተኞች በክፍለ ከተማው ወይም በወረዳው ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ውስጥ ባሉ የስራ መደቦች በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት በመመደብ ወይም በማዘዋወር ሊያሰራ ይችላል፤
7 የፓራሚሊተሪውን፣ የባለሙያዉን፣ የአመራሩን አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ስልቶችን ይቀይሳል፣ ተገቢውን ሥልጠናና ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
8 ግብረ ኃይል ያደራጃል፣ ይመራል፤ ያስተባብራል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
9 በራሱና በወረዳው ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ያገኛቸዉን መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ እንደ አስፈላጊነቱም ለሌሎች አካላት መረጃውን ያሰራጫል፤
10 በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሚቀርቡትን አስተዳደራዊ ቅጣቶች ለማስፈጸም ማስረጃዎችን በማደራጀት፣ ለክፍለ ከተማ አቃቢ ህግ ያስተላልፋል፤
11 ከወረዳዎች አቅም በላይ የሆኑ ደንብ መተላለፎች ከወረዳው ጥያቄ ሲቀርብ በመለየትና በማረጋገጥ በግብረ ሀይል እርምጃ ይወስዳል
12 የተፈፀመ ደንብ መተላለፍ በተለያዩ ምክንያት ወረዳው እርምጃ ያልወሰደበትን ጥናት በማድረግ በግብረ ሀይል እርምጃ ይወስዳል
13 ከደንብ ተላላፊዎች የሚወረሱ ንብረቶችን በፋይናንስ አሰራር ስርዓት መሰረት ያስወግዳል
14 በወረዳዎች የመሰበሰቡ ገንዘቦችና ንብረቶች በአግባቡ እየተስተዳደሩ መሆኑን ኦዲት እንዲደረግ ያደርጋል
15 ሌሎች ከከተማው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
በፅ/ቤት ሃላፊ ስር የሚገኙ ባለሙያዎች
1.የደንብ መተላለፍ ቅ/መና/ስ/ስራዎች አስተባባሪ
አቶ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሔር
የደንብ መ/ቅ/መ/ስ/ስራዎች አስተባበሪ
የአቶ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሔር መልክዕት፡-በክፍለ ከተማችን የደንብ መተላለፎች እንዳይፈፀሙ ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ስራዎችን በመስራት እንዲሁም ህገ-ወጥነትን በመከላከልና እርምጃ በመውሰድ የከተማዋን ገፅታ ለመቀየር ተግተን በመስራት እና የህዝብ አገልጋዮች ህዝብን ማገልገል ታላቅ ክብር መሆኑን ተረድተን ተገልጋዩን ህብረተሰብ በታማኝነትና በቅንነት እናገለግላለን፡፡
1 ከእስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ የተጠቃለለ ዓመታዊ የስራ ፕሮግራምና የበጀት ዕቅድ ያዘጋጃል ፡፡
2 የፅ/ቤቱን ተግባራት በማቀድ፣በማደራጀት፣በመቆጣጠር በማስተባርና በመምራት ያግዛል፡፡
3 ከባለድርሻና አደረጃቶች ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠንከር የቅድመ መከላከል ስራዎችን መስራት
4 የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማሰድ ልምድ ልውውጥ በማከናወን የቅድመ መከላከል ስራዎችን ማጠናከር
5 የብልሹ አሰራር ማክሰሚያ ሰነድ በማዘጋጀት ስልጠናዎችን መስጠት
6 የክፍለ ከተማውን መረጃ በአግባቡ ማደራጀትና ለሚፈለገው አላማ ማዋል
7 በክፍለ ከተማው የተሰራውን ዋና ዋና ተግባራት በማእከል ካለው ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በመናበብ ሪፖርት ማቅረብ
2.የግንዛቤ ማስጨበጥ ቡድን
ተጠሪነቱ ለስራ አስተባባሪዎች ሲሆን በስሩ ሶስት የስራ ከፍሎች ማለትም የግንዛቤ ማስጨበጥ ፤የስልጠናና የመረጃ ባለሙያዎችን ያካትታል
አቶ ታሪኩ ተስፋዬ
የግንዛቤ ማስጨበጥ ቡደን መሪ
የአቶ ታሪኩ ተስፋዬ መልእክት፡-በአዲሱ የመሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሰረት በተቋሙ ከተቀመጡት ስትራቴዲዊ የትኩረት መስኮች አንዱ የሆነውን ደንብ መተላለፍቅድመ-መከላከልን በዋናነት ይዞ ደንብ መተላለፍን በራሱ የማይፈፅምና የሚከላከል ማህበረሰብን መፍጠር ነው፡፡ይህንን ከግብ ለማድረስ ሦስት ዓላማዎችን በትኩረት ይዞ በመስራት ላይ እንገኛለን፤አንደኛው ለህብረተሰብ ግንዛቤ በመስጠት ደንብ መተላለፍን የመከላከል ተሳትፎን ማሳደግ በትጋት እሰራለሁ፡፡
1 የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን
2 ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ስራዎችን በመድረክ መስራት
3 በጎ ፍቃደኞችን በማስተባባር በቅድመ መከላከል ተግባር ውስጥ ማሳተፍ
4 ወረዳ ያሉ የቅድመ መከላከል ባለሙያዎች ስራዎችን በየጊዜው የድጋፍና ክትትል ስራዎችን በመስራት መደገፍ
5 የተለያዩ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤን ማሳደግ
3.የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር ኢንስፔክሽን ቡድን
ተጠሪነቱ ለፅ/ቤቱ ሃላፊ ሲሆን በስሩ አራት ባለሙያዎችን መደን ይጠይቃል ነገር ግን ተመድበው ያሉት ሶስት ናቸው፡፡
ሻምበል ታገሰ
የደንብ መተላለፍ ቁጥጥርና ኢንስፒክሽን ቡድን መሪ
የሻምበል ታገሰ መልዕክት፡-በክፍለ ከተማችን ውስጥ የሚገኑ የደንብ ጥሰቶች በመከላከልና በመቆጣጠር እንዲሁም እርምጃ በማስወሰድ ኢንስፔክሽ በማድረግ ክፍለ ከተማችን የደንብ ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ በትኩረት እሰራለሁ፡፡
የሚያከናዉናቸዉ ዋና ዋና ተግባራት፡-
1 የደንብ ጥሰቶችን መሰረት ያደረገ ጥናት በማጥናት ስራዎች እንዲሰሩ ማድረግ
2 የተሻሉ አሰራሮችን በመውሰድ የልምድ ልውውጥና ምርት ተሞክሮን ማስፋት
3 በግብርሀይል የሚወሰድባቸውን መረጃዎችን ማሰባስብ
4 በመስክ ደንብ መተላለፎችን ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ የክትትልና ቁጥጥር ተግባራትን ማከናወን
5 በመስክ ምልከታ በክትትልና ቁጥጥር ወቅት የታዩ የአሰራር ክፍተቶችን መለየት
6 በተፈጸሙ የደንብ መተላለፎች ላይ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት በመስክ መረጃዎችን ማጣራት
7 በእርምጃ አወሳሰዱ ላይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማወያት፤ የኦፕሬሽን ዕቅድ ማዘጋጀትና መግባባት መፍጠር
8 ለእርምጃ አወሳሰድ አጋዥ የሆኑ ሎጄስቲክ ማዘጋጀት
9 የኦፕሪሽን እርምጃ አወሳሰድ ሂደቱን መገምገም & ሪፖርት ማድረግ
4.የግብረ-ኃይል ቡድን
አቶ ጋዲሳ ብሩ
ተጠሪነቱ ለፅ/ቤቱ ሃላፊ ሲሆን በስሩ ሁለት ሽፍት መሪና ሁለት ሰርቪሊያንስ መሪዎች አሉት፡፡
1 አፍራሽ ግብረ-ሃይል ጋር በመቀናጀት በደንብ ተላለፊዎች ላይ እርምጃ መውሰድ
2 በግብረ-ሃይል የተወረሱ ንብረቶች በክ/ከተማው ንብረት ክፍል ማስገባት
3 የግብረ-ሃይል እርምጃ አወሳሰድ ሂደቱን መገምገም & ሪፖርት ማድረግ
4 የፓትሮል ስምሪት አሰራርን ስልት መንደፍ
5 በፓትሮል ደንብ መተላለፍ ላይ እርምጃ አወሳሰድ ወቅት የተለዩ ክፍተቶችን ማስተካከያ ማድረግ